am_tn/gen/50/15.md

2.3 KiB

ምናልባት ዮሴፍ ቂም ሊበቀለን ይሆናል

እዚህ ቂም ዮሴፍ በእጁ እንደምይዝ ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል አት ምናልባት ዮሴፍ የጠላን ይሆናል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ባደረግንበት ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል

እርሱን የበደለውን ሰው መበቀል አንድ ሰው ከሌላ ሰው የተበደረውን እንደመመለስ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “ባደረግንበት ክፋት ምናልባት ልበቀለን ይችላል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

አባትህ ገና ሳይምት እንዲህ ብሎ አዝዞአል ዮሴፍን እንዲህ በሉት እባክህ የወንድምችን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና

ይህ ሁለት ደረጃና ሶስት ደረጃ ጥቅስ ይዞአል እንደተዘዋዋሪ ጥቅስም ሊገለጹ ይችላሉ:: አት “አባትህ ከመሞቱ በፊት እኛ የበደልንህን ይቅር እንዲትለን እንድንነግርህ አዝዞናል” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

አባትህ ከመሞቱ በፊት አዝዞናል እንዲህ ስል

ያዕቆብ ለወንድማማቾች ሁሉ አባት ነው:: እዚህ ዮሴፍ አባቱ ለተናገረው ትኩረት እንዲሰጥ “አባትህ” ብለው ይናገራሉ:: አት “አባታችን ከመሞቱ በፊት”

በበደሉህ ጊዜ ያደረጉትን ኃጢአታቸውን

በአንተ ላይ ስላደረጉት ክፉ ነገሮች

አሁንም

ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው

የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል

ወንድሞቹ ራሳቸውን “የአባትህ አምላክ ባሪያዎች” ብለው ይገልጻሉ:: (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

ዮሴፍ ይህን ስሉት አለቀሰ

የሴፍ ይህን መልእክት በሰማ ጊዜ አለቀሰ