am_tn/gen/50/10.md

1.3 KiB

እነርሱም በመጡ ጊዜ

“እነርሱ” የሚለው ቃል በቀብር ሥነሥርዓቱን ይካፈሉ የነበሩ ሰዎችን ያመለክታል

የአጣድ አውድማ

ተገቢ ትርጉሞች 1) “አጣድ” የሚለው ቃል እሾህ ማለት ነው፤ አናም እጅግ ብዙ እሾሆች የሚበቅሉበት መሬት ሊባል ይችላል ወይም 2) “የአውድማው ባለቤት ስም ሊሆን ሊችላል:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ከፍተኛና መራራ ለቅሶ አለቀሱ

እጅግ መራራና ከፍተኛ ልቅሶ አልቅሰው ነበር

ሰባት ቀን

7 ቀን (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

በአጣድ አውድማ

ተገቢ ትርጉሞች 1) አጣድ የተባለው ሰው አውድማ ውስጥ ወይም 2) አጣድ በተባለው አውድማ ውስጥ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ይህ ግብጻዊያን እጅግ ያዘኑበት ጊዜ ነበር

የግብጻዊያን ልቅሶ መራራ ነበር

አቤል ምጽራይም

ተርጓሚዎች የሚከተለውን እንደ ግርጌ ማስታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ አቤል ምጽራይም የሚለው ስም የግብጻዊያን ሐዘን ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)