am_tn/gen/48/14.md

2.5 KiB

ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ

ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማኖር እርሱ ትልቅ በረከት እንዲቀበል ምልክት ነበር (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

እስራኤል ዮሴፍን ባረከው

ዮሴፍ ደግሞ ኤፍሬምንና ሚናሴን ይወክላል:: ዮሴፍ አባት ስለሆነ እርሱ ብቻውን ተጠቅሶአል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እግዚአብሔር

እግዚአብሔርን ማገልገል በእግዚአብሔር ፊት እንደመሄድ ተደርጐ ተነግሮአል አት አያቴ አብርሃምና አባቴ ይስሐቅ ያገለገሉት እግዚአብሔር (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እረኛ የሆነኝ

እረኛ በጐቹን እንደምንከባከብ እግዚአብሔር እስራኤልን ተንከባክቦታል አት እረኛ እንስሳትን እንደሚንከባከብ የተንከባከበኝ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

መልአክ

ተገቢ ትርጉሞች አት እግዚአብሔር ያዕቆብን ለመጠበቅ የላከውን መልአክ ያመለክታል 2 ይህ እግዚአብሔር ያዕቆብን ለመጠበቅ በመልአክ መልክ የተገለጸውን ያመለክታል

ጠበቀኝ

አዳነኝ

ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በእነርሱ ይጠራ

እዚህ ስም ሰውን ይወክላል ስሜ በእነርሱ ይጠራ የሚለው ሀረግ አንድ ሰው ከሌላ ሰው የተነሣ እንዲታወስ የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከኤፍሬምና ሚናሴ የተነሣ ሰዎች አብርሃም ይስሐቅንና እኔን ያስታውሱ” (ምትክ ቃል : ፈሊጣዊ አነጋገርና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

በምድርም ላይ ይብዙ

እዚህ እነርሱ ኤፍሬምንና ሚናሴን ቢያመለክትም የእነርሱ ትውልድንም ይወክላል:: አት “በምድር ሁሉ ላይ የሚኖር ብዙ ትውልድ ይኑራቸው” (ምትክ ቃል እጠቃቀም ይመልከቱ)