am_tn/gen/47/29.md

2.1 KiB

እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን

ይህ ጊዜ እንደሚጓዝና አንድ ቦታ እንደሚመጣ ይናገራል:: አት “እስራኤል የሚሞትበት ጊዜ እንደደረሰ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

በዓይኖችህ ፊተ ሞገስን ካገኘሁ

እዚህ ዓይኖች የማየት ምትክ ቃል ነው እናም ማየት ሃሳብን ወይም አመለካከትን ይወክላል:: አት “በአንተ ፊት ሞገስ ካገኘሁ ወይም ካስደሰትኩህ” (ምትክ ቃላትና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

አሁን

ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ለሚቀጥለው ጠቃሚ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው

ሞገስ ማግኘት

አንድ ሰው በአንድ ሰው ተቀባይነቱን ማረጋገጥ ማለት ነው ፈሊጣሊ አነጋገር ይመልከቱ

እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ

ለጠንቃቃ ቃል መግባት የሚደረግ ምልክት ነው በዘፍጥረት 24:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

በጐነትንና ታማኝነትን ሊታደርግልኝ

በጐነት እና ታማኝነት የተባሉ ረቂቅ ስሞች እንደ ቅጽል ስሞች ሊተረጐሙ ይችላሉ አት በበጐነትና በታማኝነት አድርግልኝ ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ

እባክህን በግብጽ አትቅበረኝ

እባክህን የሚለው ለዚህ ጥያቄ እጽንዖት ይሰጣል

ከአባቶቼ ጋር ሳንቀላፋ

ማንቀላፋት መሞትን ለዘብ ባለ ቃል የሚገልጽ ነውፀፀ አት “በሚሞትበትና ከዚህ ቀደም የሞቱ ቤተሰቦቼን በሚገናኝበት ጊዜ” (ንኀብነት ወይም ለዘብ ባለና በተዘዋዋሪ መንገድ አንድን ነገር የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ቃል ግባልኝ

“ተስፋ ስጠኝ” ወይም “ማልልኝ”

ማለለት

“ተስፋ ሰጠው” ወይም “ቃል ገባለት”