am_tn/gen/46/33.md

1.8 KiB

እንዲህም ሆነ

ይህ ሀረግ የተጠቀመው በታሪኩ ስለተከሰተው ዋና ክስተት ለማመልከት ነው፡፡ በቋንቋዎ ይህንን የሚገልጹበት መንገድ ካለ የጠቀሙ

ሥራችሁ ምንደነው ብሎ ቢጠይቃችሁ

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል:: ይህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ምን ሥራ ታከናውናላችሁ ብሎ ቢጠይቃችሁ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

እንዲህ በሉት እኛ ባሪያዎችህ…. እኛም አባቶቻችንም…

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል:: ይህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እንዲህ በሉት….እኛና አባቶቻችን ሁላችን…” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

የአንተ ባሪያዎች

የዮሴፍ ቤተሰቦች ለፈርዖን ሲናገሩ ራሳቸውን ባሪያዎችህ ብለው ማቅረብ አለባቸው:: ይህ ለአንድ ታላቅ ባለሥልጣን የሚነገርለት መንገድ ነው:: ይህም እንደ አንደኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኛ አገልጋዮችህ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጻዊያን ርኩስ/ ጸያፍ ነውና

“ጸያፍ” የሚለው ረቂቅ ስም “የሚያስጠላ” በሚለው ቅጽል ስም ሊተረጐም ይችላል:: አት “ግብጻዊያን የከብት ጠባቂዎችን እንደ ጸያፍ ይቆጥሩ ነበር” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)