am_tn/gen/45/16.md

2.1 KiB

በፈርዖን ቤት የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: እንዲሁም ደግሞ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “የዮሴፍ ወንድሞች እንደመጡ በፈርዖን ቤተመንግሥት ያለው ማንኛውም ሰው ሰማ” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅስ እናም ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

የፈርዖን ቤት

የፈርዖንን ቤተመንሥት ይወክላል

ለወንድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ይህን አድርጉ አህዮቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከነዓን ምድር ሂዱ፤ አባታችሁንና ቤተሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብጽ ምድር እሰጣችኋለሁ፤ የምድርቱንም ስብ/በረከት ትበላላችሁ፡፡

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: አት “አህዮቻቸውን እንዲጭኑና ወደ አባታቸውና ቤተሰቦቻውው ወደ ከነዓን እንዲሄዱ ለወንድሞችህ ንገራቸው፤ ወደዚህ እንዲመጡና እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብጽ ምድር እንደሚጣቸወ፤ የምንሰጠውን በረከት እንደሚመገቡ ደግሞም ንገራቸው” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅስ ይመልከቱ)

እኔም መልካም ከሆነው የግብጽ ምድር እሰጣችኋለሁ፤

እኔም እጅግ ለም የሆነውን የግብጽ ምድር እሰጣችኋለሁ

የምድርቱንም ስብ ትበላላችሁ

ምድርቱ የሚትሰጠው መልካም እህል እንደ ምድሪቱ ስብ ተደርጐ ተቆጥሮአል:: አት “የምድሪቱንም እህል ትመገባላችሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)