am_tn/gen/45/04.md

1.3 KiB

ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ

ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አት “ወደ ግብጽ ላመጡኝ ነጋዴዎች እንደ ባሪያ የሸጣችሁኝ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አትዘኑ

“አትቈጩ” ወይመ “አትጨነቁ”

ወደዚህ ስለሸጣችሁኝ

ትርጉሙም በግልጽ ሊነገር ይችላል፡፡ አት “እንደ ባሪያ ሸጣችሁኝ እናም ወደ ግብጽ ምድር ላካችሁን”

ሕይወት ለማዳን

እዚህ “ሕይወት” ዮሴፍ በረሃቡ ጊዜ ያዳናቸውን ሰዎች ይወክላል:: አት “የብዙ ሰዎችን ሕይወት እንዳድን” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና አሉ

የማይታረስባቸው ወይም ሰብል የማይሰበሰባቸው አምስት ዓመታት አሉ እዚህ የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበስብባቸው ሰብሎች ከድርቁ የተነሣ እንደማይመረቱ የሚገልጹ ናቸው:: አት “ረሃቡ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ይቀጥላል” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)