am_tn/gen/44/30.md

3.4 KiB

አሁን

ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ጠቃሚ ነገር ትኩረት እንዲሰጥበት ተጠቅሞአል

እንግዲህ በምንመለስበት ጊዜ … በሐዘን ወደ መቃብር

ይሁዳ ያለ ብንያምን ወደ አባቱ በሚመለስበት ጊዜ ምን ሊፈጠር እንደሚችል የሚገምተውን ነገር ግን እውነት የሆነውን ለዮሴፍ ይገልጻል (ግምታዊ ሁኔታዎችን ይመልከቱ)

ወደ ባሪያህ በሚመጣበት ጊዜ

እዚህ “መምጣት” “መሄድ” ወይም “መመለስ” በሚለው መተርጐም ይችላል::

ብላቴናው ከእኛ ጋር አለመኖር

ልጁ ከእኛ ጋር አለመኖር

ሕይወቱ ከልጁ ሕይወት ጋር የተሣሠረ ስለሆነ

አባታቸው ልጁ ከሞቴ እሞታለሁ ያለው አባባል የሁለቱ ሕይወት በአካል በጥብቅ የተሣሠረ እንደሆነ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “እርሱም ልጁ ካልተመለሰ እሞታለሁ ስላለ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እንዲህም ሆነ

ይሁዳ ወደፊት ይሆናል ብሎ ስለሚገምተው ነገር በእርግጥ እደሚደረግ አድርጐ ይናገራል (ግምታዊ ሁኔታዎች ይመልከቱ)

ባሪያዎችህ የባሪያህን የአባታችንን ሽበት በሐዘን ወደ መቃብር ያወርዳሉ

ወደ መቃብር ማውረድ እንዲሞትና ወደ መቃብር እንዲወርድ ማድረግ ማለት ነው:: “ማውረድ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው መቃብር በመሬት ውስጥ እንደሆነ በተለምዶ የታወቀ ስለሆነ ነው:: አት “እናም ሽማግሌውን አባታችንን በሐዘን እንዲሞት እናደርጋለን” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ባሪያዎችህ ወይም አገልጋዮችህ

ይሁዳ ራሱንና ወንድሞችን “ባሪያዎችህ” ብሎ ያመለክታል:: ይህ ለአንድ ትልቅ ባለሥልጣን መደበኛ መንገድ የሚነገርለት ነው:: አት “እኛ አገልጋዮችህ” ወይም “እናም እኛ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገንነ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

የባሪያህን የአባታችንን ሽበት

እዚህ “ሽበት” ያዕቆብን የሚወክልና ሽምግልናውን የሚናገር ነው:: አት “ሽማግሌው አባታችን” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ) ስለ ልጁ ደኀንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ ረቂቅ ስም ዋስ ተስፋ በሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል አት ልጁን በሚመለከት ለአባቴ ተስፋ ስጥቼዋለሁ ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ

ባሪያህ

ይሁዳ ራሱን “ባሪያህ” ብሎ ያመለክታል፡፡ አት “ለእኔ ለባሪያህ” ወይም “ለእኔ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

በአባቴ ፊት በደሌን እሸከማለሁ

እንደበደለኛ መቆጠር በደል እንድሰው የሚሸከመው ነገር ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “አባቴ ይወቅሰኛል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)