am_tn/gen/44/23.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይሁዳ ታሪኩን ለዮሴፍ መናገር ቀጠለ

ከዚያም ባሪያዎችህን እንዲህ አልሄን፤ ታናሽ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ጋር ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከዚያም ለባሪያዎችህ ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልመጣ ፊቴን አታዩም አልሄን ” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

ከዚያም ለባሪያዎችህ አልህ

ይሁዳ ራሱንና ወንድሞቹን እንደ “እርሱ ባሪያዎች” ያመለክታል፡፡ ይህ ትልቅ ባለሥልጣን ለሆነ ለአንድ ሰው የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው፡፡ (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)

ይዞ መውረድ …ወደ ታች መውረድ

ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ ሲነገር መውረድ የሚለው ቃል የተለመደ ነው::

ዳግመኛ ፊቴን አታዩም

እዚህ “ፊት” ሙሉ ሰውን ይወክላል:: አት እንደገና አታዩኝም (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

ከዚያም እንዲህ ሆነ

ይህ ሀረግ የተጠቀመው የታሪኩ አድስ ክፍል መጀመሩን ለማመለከት ነው:: በቋንቋዎ ይህን የሚገልጹበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ:: (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)

ወደ ባሪያህ ወደ አባታችን በወጣን ጊዜ

ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ ሲነገር “ወደ ላይ መውጣት” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው

የጌታዬን ቃል ነገርነው

ይሁዳ ዮሴፍን እንደ “ጌታዬ” ያመለክታል:: አት ጌታዬ የነገርከውን ቃል ነገርነው”(አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)

አባታችን ‘ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱልን አለ’

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አባታችን አንደገና ወደ ግብጽ በመሄድ ለእኛና ለቤተሰቦቻችን እህል እንድንሸምት ተናገረን ” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

እኛም አልነው ‘መሄድ አንችልም ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር…’

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከዚያም ለእርሱ ወደ ግብጽ መውረድ አንችልም አልን ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር … ከእኛ ጋር ” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

የሰውየውን ፊት ማየት

እዚህ ፊት ሙሉ ሰውን ይወክላል:: አት “ሰውየውን ለማየት” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)