am_tn/gen/44/20.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በዮሴፍ ፊት መናገሩን ይሁዳ ቀጠለ

እኛም ለጌታዬ እንዲህ አልን ‘ሽማግሌ አባት አለን …. አባቱም ይወድደዋል’

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እናም እኛ እንዲህ አልን ‘አባት አለን አባቱም ይወድደዋል’” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

ለጌታዬ እንዲህ አልን

ይሁዳ ዮሴፍን እንደ “ጌታዬ” ያመለክተዋል:: ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: አት “ጌታዬ እኛም እንዲህ አልን”(አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)

አባቱም ይወድደዋል

ይህ ለጓደኛ ወዳጅ ወይም ለቤተሰብ አባል ያለውን ፍቅር ይገልጻል

ከዚያም ለባሪያዎችህ ወደእኔ አምጡት እኔም አየዋለሁ እልህ

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እናም አንተ ለባሪያዎችህን ታናሽ ወንድማችሁን አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ’” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

ከዚያም ለባሪያዎችህ እንዲህ አልህ

ይሁዳ ወንድሞቹንና ራሱን እንደ እርሱ ባሪያዎች ያመለክታል:: አት “ከዚያም ለእኛ ለባሪያዎችህ እንዲህ አልህ”(አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)

ወደ እኔ ይዛችሁ ውረዱ

ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ ሲነገር መውረድ የሚለው ቃል የተለመደ ነው:: አት “ወደ እኔ አምጡት” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ከዚያም በኋላ ጌታዬን አልነው “ብላቴናው… አይሆንለትም …አባቱ ይሞታልና”

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “መልሰን እኛም ለጌታዬ ልጁ ….አይችልም፤ ….አባትየው ይሞታል” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

አባትዬው ይሞታል

ከማዘን የተነሣ አባታቸው እንደሚሞት ይገልጻል (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)