am_tn/gen/44/18.md

2.7 KiB

ቀረብ ብሎ

ተጠግቶ

እኔ አገልጋይህ

ይሁዳ ራሱን እንደ “አገልጋይህ ወይም ባሪያህ” ያመለክታል:: ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: ይህ በአንደኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኔ ባሪያህ ወይም አገልጋይህ”(አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃል እንድናገር

“ጆሮ” የሚለው ለሙሉ ሰው የሚሆን ምትክ ቃል ነው፡፡ አት “ጌታዬ ሊናገርህ” (ምትክ ቃል አጠቃቀም ይመልከቱ)

በጌታዬ ጆሮ

እዚህ ጌታዬ ዮሴፍን ያመለክታል፡፡ ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: ይህ በሁለተኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ለአንተ”(አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

እኔን አገልጋይህን ቁጣህ አያቃጥለኝ

መቆጣት እንደሚያቃጥል እሳት ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “አባክህን እኔን አገልጋይህን አትቆጣኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

አንተ እንደፈርዖን ነህና

ጌታው ትልቅ ሥልጣን እንዳለው ትኩረት ለመስጠት ከፈርዖን ጋር ያወዳድረዋል:: ይህም የሚገልጸው ሊቆጣውም ሊገድለውም እንደሚችል ነው አት “እንደ ፈርዖን ኃይለኛ ስለሆንህና ወታደሮችህም ሊገድሉኝ ስለሚችሉ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቀ መረጃ ይመልከቱ)

ጌታዬ ባሪያዎቹን፤ “አባት አላችሁ ወይም ወንድም?”ብሎ ጠየቀ::

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ጌታዬ አባት ወይም ወንድም እንዳለን ጠየቀን” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

ጌታዬ ባሪያዎቹን ጠየቀ

ይሁዳ ዮሴፍን “ጌታዬ” እና “እርሱ” በሚሉ ቃላት ያመለክተዋል:: አንዲሁም ደግሞ ወንድሞቹንና ራሱን እንደ “የእርሱ ባሪያዎች” ይገልጻል:: አት “አንተ ጌታዬ ባሪያዎችህን ጠየቅሄን ወይም አንተ ጠቀየቅሄን” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)