am_tn/gen/43/32.md

2.6 KiB

አገልጋዮችም ለዮሴፍ ለብቻው ለወንድሞቹም ለብቻቸው አቀረቡላቸው:: ከእርሱ ጋር ለሚበሉ ግብጻዊያን ደግሞ ለብቻቸው አቀረቡላቸው::

ይህም ዮሴፍ ወንድሞቹና ሌሎች በአንድ ክፍል በተለያየ ቦታ ተቀምጠው ይመገባሉ ማለት ነው አገልጋዮችም ለዮሴፍ ለብቻው ለመንድሞቹም ለብቻቸው እናም ከእርሱ ጋር ለሚበሉ ግብጻዊያን ደግሞ ለብቻቸው አቀረቡላቸው

ከእርሱ ጋር ለሚበሉ ግብጻዊያን ለብቻቸው

እነዚህ ምናልባት ከእርሱ ጋር የሚበሉ የግብጽ ባለሥልጣናት ይሆናሉ ነገር ግን ከዮሴፍና ከዕብራዊያን ወንድሞቹ ተለይተው ተቀምጠዋል

ግብጻዊያን ከዕብራዊያን ጋር መመገብ አይሆንላቸውም ምክንያቱም ያ ለግብጻዊያን መርከስ ነውና

ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል ይህንን ያደረጉበት ምክንያት ግብጻዊያን ከዕብራዊያን ጋር መመገብ ጸያፍ አድርገው ያስባሉ

አብረው እንጀራ አይበሉም

እዚህ እንጀራ ጠቅላላ ምግብ ይወክላል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ወንድምቹ በእርሱ ፊት ተቀመጡ

እያንዳንዱ ወንድም የት መቀመጥ እንዳለበት ዮሴፍ እንዳዘጋጀ ሊገመት ይገልጻል የተገለጸውን መረጃ ግልጽ ማድረግ ይቻላል አት የሚቀመጡበት ቦታ በተዘጋጀላቸው መሠረት በሰውየው/ዮሴፍ ፊት ወንድሞቹ ተቀመጡ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)

በፊቱም በኩሩ እንደታላቂነቱ ታናሹም እንደታናሽነቱ

“በኩር”ና “ታናሽ” የተጠቀሙት ሁሉም ወንድሞች በአንድነት እንደየዕድሜያቸው በተርታ እንደተቀመጡ ለመግለጽ ነው::( ነጠላ ነገር በብዙ የመግለጽ ዘይቤ/merism/ ይመልከቱ)

ሰዎቹም/ወንድሞቹም በአንድነት ተገረሙ

ይህን ባወቁ ጊዜ ሰዎቹ በጣም ተገረሙ

የብንያም ድርሻ ከሌሎች ወንድሞች አምስት እጥፍ ነበር

አምስት እጥፍ የሚለው ሀረግ በአጠቃላይ ብዙ በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት “ብንያም የተቀበለው ድርሻ ወንድሞቹ ከተቀበሉት በጣም ብዙ ነበር”