1.3 KiB
1.3 KiB
አገልጋይህ አባታችን
አባታቸውን እንደ “አገልጋይህ” ማመልከታቸው አክብሮታቸውን ለማሳየት ነው አት “አባታችን የሚያገለግልህ”
አጐንብሰው ሰገዱለት
እነዚህ ቃላት በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው በሰውየው ፊት ጐንበስ በማለት አክብሮታቸውን ገለጹ:: አት “በፊቱ ሰገዱለት” (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ዮሴፍም ዐይኑን ሲቃኝ
ቀና ብሎ ሲመለከት ማለት ነው ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ
የእናቱን ልጅ እናም አለ
ይህ በአድስ ዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “የእናቱን ልጅ.. አየ:: ዮሴፍም አለ፤”
ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን?
ተገቢ አማራጭ ትርጉሞች 1 ይህ ሰው ብንያምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ዮሴፍ በውኑ ይጠይቃቸዋል ወይም 2) ይህ አግናኝ ጥያቄ ነው:: “ደግሞ ይህ ታናሽ ወንድማችሁ …. “ (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ልጄ
ይህ አንድ ሰው በዝቅተኛ ደረጃ ላለ ሌላ ሰው በጓደኝነት መንገድ የሚጠራው አጠራር ነው:: አት “ወጣቱ”