am_tn/gen/43/06.md

2.0 KiB

ለምን በደላችሁኝ?

ለምን ይህ ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?

ሰውየው አጥብቆ ጠየቀን

ሰውየው ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀን

ስለእኛ

እዚህ እኛ የሚለው በተለይ የሚያመለክተው ወደ ግብጽ የወረዱና ከሰውየው ጋር የተነጋገሩ ወንድሞችን ነው

አባታችሁ አሁን በሕይወት አለ? ሌላ ወንድም አላችሁ? ሲል ጠየቀን

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል አት አባታችን በሕይወት እንዳለና ሌላ ወንድም እንዳለን በቀጥታ ጠይቆናል:: (በጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

እኛም ለጥያቄዎቹ መልስ ሰጠን

የጠየቀንን ጥያቄዎች መለስንለት

…ይዛችሁ እንዲትመጡ እንደሚለን እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?

ሰውየው ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደሚነግር ልጆቹ አለማወቃቸውን አጽንተው ለመንገር ጥያቄ ይጠቀማሉ ይህ አግናኝ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል አት እንደዚህ … እንደሚለን አላወቅንም ነበር (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ወንድማችሁን ይዛችሁ ውረዱ ወይም አምጡ እንደሚለን

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል አት ወንድማችንን የዘን ወደ ግብጽ እንድንወርድ እንደሚነግረን (በጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

ወንድማችሁን ይዛችሁ ውረዱ

ከከነዓን ወደ ግብጽ ጉዞ በሚነገርበት ጊዜ “ወደታች መውረድ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው