am_tn/gen/43/03.md

1.8 KiB
Raw Permalink Blame History

ይሁዳ እንዲህ አለው

ይሁዳ ለአባቱ ለያዕቆብ እንዲህ አለው

ያ ሰው

ይህ ዮሴፍን ነው የሚያመለክተው ነገር ግን ወንድምቹ ዮሴፍ መሆኑን አላወቁትም ነበር:: እነርሱም እርሱን ያመለከቱን እንደ “ያ ሰው” ወይም በዘፍጥረት 42:3 እንደተነገረው “ያ ሰው የምድሪቱ ጌታ” ነው::

ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ፊቴን አታዩም ብሎ አስጠንቀቆናል

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል ይህም እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ታናሽ ወንድማችንን ይዘነው ካላመጣን ፊቱን ማየት እንደማንችል አስጠንቅቆናል” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

በጥብቅ አስጠንቅቆናል

እንዲህም በማለት በጥብቅ አስጠንቀቆናል

ፊቴን አታዩም

ወደ ግብጽ አገር ያለ ብንያም መመለስ እንደማይችሉ ለአባቱ ለማጽናት በዘፍጥረት 43፡ 4-5 ይሁዳ ይህን ሀረግ ሁለት ጊዜ ይጠቀማል:: ፊቴን የሚለው የዚያ ሰው የዮሴፍ ፊት ያመለክታል:: አት “ፊቴን አታዩም” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዜይቤ ይጠቀሙ)

ወንድማችን ከእኛ ጋር

ይሁዳ ራሔል ከመሞትዋ በፊት የወለደችውን የመጨረሻ ልጅ ብንያምን ያመለክታል

እኛም ወደዚያ አንወርድም

ከከነዓን ወደ ግብጽ ጉዞ በሚነገርበት ጊዜ “ወደታች መውረድ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው