am_tn/gen/42/05.md

1.5 KiB

የእስራኤል ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡበት ጋር

“መጡ” የሚለው ቃል “ሄዱ” በሚለው ሊተረጐም ይችላል:: እንዲሁም እህል እና ግብጽ የተባሉ ቃላት የታወቁ ናቸው:: አት “የእስራኤል ልጆች እህል ለመሸመት ከሌሎች ሰዎች ጋር ወደ ግብጽ ሄዱ” (ሄደ እና መጣ አጠቃቀምና ድብቅ ቃላት የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

በዚህን ጊዜ ዮሴፍ

“በዚህን ጊዜ” ታሪኩ ወደ ዮሴፍ ሕይወት መረጃ መቀየሩን ያመለክታል:: (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)

በምድሪቱ ላይ

ምድር ግብጽን ያመለክታል:: አት “በግብጽ ላይ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ለአገሩ ሰዎች ሁሉ

እዚህ አገር ግብጽንና ዙሪያው ያሉ አገሮችን ያጠቃልላል አት እህል ለመሸመት ከተለያዩ አገሮች ለመጡ ሰዎች ሁሉ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

የዮሴፍም ወንድሞች መጡ

“መጡ” እንደ “ሄዱ” ሊተረጐም ይችላል:: (መጣ እና ሄደ አጠቃቀም ይመልከቱ)

በግምባራቸው ወደ ምድር ጐንበስ ብለው ሰገዱለት

ይህ አክብሮትን የመስጠት ምልክት ነው:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)