am_tn/gen/41/55.md

1.5 KiB

ራብ በመላው የግብጽ ምድር መስፋፋት ሲጀምር

እዚህ “ምድር” ሰዎችን ይወክላል:: አት “ግብጻዊያን ሁሉ በተራቡ ጊዜ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ራቡ በአገሩ ሁሉ ፊት እየተስፋፋ ስለሄደ

እዚህ ፊት የሚለው ቃል ምድር ላይ ማለትን ያመለክታል:: አት “ራቡ በየአገሩ ተስፋፋ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ዮሴፍ ጐተራዎችን ሁሉ ከፍቶ እህሉ ለግብጻዊያን እንዲሸጥ አደረገ

እዚህ “ዮሴፍ” የዮሴፍን አገልጋዮች ይወክላል:: አት “ዮሴፍ አገልጋዮቹ ጐተራዎችን ሁሉ እንዲከፍቱና ለግብጻዊያን እህል እንዲሸጥ አደረገ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ከምድር ሁሉ ወደ ግብጽ ይመጡ ነበር

እዚህ ምድር ከሁሉ አገራት የሆኑ ሰዎችን ይወክላል:: አት “በዙሪያው ካሉ አገሮች ሁሉ ሰዎች ወደ ግብጽ ይመጡ ነበር” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

በምድር ሁሉ

በመላው ምድር በግብጻዊያንን የንግድ መሥመሮች የሚጠቀሙ በድርቅ የተጠቁ የተለያዩ የንግድ አጋሮችና አገሮች ሁሉ ወደ ግብጽ ይመጡ ነበር እንደማለት ነው