am_tn/gen/41/42.md

1.7 KiB

ፈርዖንም ባለማኀተሙን ቀለበት አውልቆ …. የወርቅ ሐብል አጠለቀለት

እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች የሚያመለክቱት ዮሴፍ ያቀደውን ሁሉ እንዲያደርግ ፈርዖን ለዮሴፍ ሥልጣን መስጠቱን ነው (ምልክታዊ ድርጊት የመልከቱ)

ባለማኀተሙ ቀለበት

ይህ ቀለበት የፈርዖን ማኀተም የተቀረጸበት ነው:: ይህም ያቀደውን እንዲያከናውን ለዮሴፍ ገንዘብና ሥልጣንን ሰጠው::

ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ

የተልባ እግር የተሠራ ልብስ ሰማያዊ አበባ ካለው የተልባ እግር የተሠራ ለስላሳ ጠንካራ ልብስ ነው::

የእርሱም በሆነው ሁለተኛው ሠረገላ ላይ አስቀመጠው

ይህ ድርጊት ለሰዎች ግልጽ የሚያደርገው የፈርዖን ሁለተኛ ሰው ዮሴፍ ብቻ መሆኑን ነው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

ስገዱ ወይም እጅ ንሡ

ስገዱና ዮሴፍን አክብሩ እጅ መንሣትና መስገድ ክብርንና አክብሮትን የመስጠት ምልክት ነው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

ፈርዖን በምድሪቱ ባለው ማንኛውም ላይ ሾመው

ማንኛውም ላይ ሾመው የሚለው ሀረግ ሁሉ ላይ ስልጣን ሰጠው ማለት ነው:: እዚህ ምድር ሰዎችን ያመለክታል በዘፍጥረት 41:41 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት “በግብጽ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገርና ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ)