am_tn/gen/41/33.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዮሴፍ ለፈርዖን መናገሩን ቀጠለ

አሁንም

ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ስለሚቀጥለው ጠቃሚ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው

እንግዲህ ፈርዖን … ይፈልግ

ዮሴፍ ለፈርዖን እንደ ሶስተኛ ወገን ሰው ይናገራል ይህ አክብሮትን የመግለጫ መንገድ ነው በሁለተኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አንተ ፈርዖን ፈልግ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

በግብጽ ምድር ላይም ይሹመው

ይሹመው ማለት ኃላፊነት ይስጠው ማለት ነው፡፡ አት “በግብጽ ግዛት ላይ ኃላፊነት ይስጠው ወይም በግብጽ ግዛት ላይ ይሹመው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

የግብጽ ምድር

እዚህ ምድር በግብጽ ምድር ያሉ ሰዎችንና ሁሉን ነገር ይወክላል (ተመሣሣይ ተዛማጅ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልቱ)

በግብጽ ምድር ከሚገኘው የእህል ምርት አንድ አምሰተአኛውን ይውሰዱ

አምስተኛ የሚለው ቃል ክፍልፋይ ነው:: የግብጽን ምድር እህል ምርት በአምስት መደብ ይክፈሉ፤ ከዚያም አንዱን እጅ ወይም መደብ ይውሰዱ (ክፍልፋዮችን ይመልከቱ)

በሰባት የጥጋብ ዓመታት

የተትረፈረፈ ምግብ ባለባቸው ሰባት ዓመታት