am_tn/gen/41/30.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዮሴፍ የፈርዖንን ሕልምች መተርጐም ቀጠለ

ከዚህ በኃላ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ

ወደ አንድ ቦታው ተንቀሳቅሶ እንደሚመጣ ነገር ተደርጐ ስለ ሰባት ዓመታት ራስ ተነግሮአል አት ከዚም በኋላ እጅግ ጥቂት ምግብ የሚሆንበት ሰባት ዓመታት ይሆናሉ (ዘይቤይዊ አነጋገር ይመልከቱ)

የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት … የጥጋቡ ዘመን ሁለ ጨርሶ አይታወስም::

….የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ የጥጋብ ዘመን ፈጽም ይረሳል:: ዮሴፍ ለጉዳዩ አጽንዖት ለመስጠት አንድን ሀሳብ በሁለት መንገድ ይገልጻል (ተመሣሣይ ተጓዳኝ አባባሎችን ይመልከቱ)

በግብጽ ምድር የጥጋብ ዘመን ሁሉ ይረሳል

ምድር ሰዎችን ያመለክታል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “የግብጽ ሰዎች የተትረፈረፈ ምግብ የነበረበትን ዓመታት ሁሉ ይረሳሉ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤና ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

አገሪቱን ይጐዳሉ

አገር የሚለው የአገሪቷን መሬት ሰዎችና መላውን የአገሪቷን አካል ያመለክታል (ምትክ ቃላትን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ከሚመጣው ራብ የተነሣ

ይህ ተከትሎ እንደሚመጣ እንደ አንድ ነገር ስለሚመጣው ራብ ወይም ድርቅ ይናገራል፡፡ አት “ከዚያ በኋላ በሚሆነው ራብ ወይም ድርቅ የተነሣ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ሕልሙ ለፈርዖን በሁለት መልክ በድጋሚ መታየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለሆነ ነው

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እግዚአብሔር ሁለት ሕልሞችን የሰጠህ ነገሮች በእርግጥ እንደሚከሰቱ ለማሣየት ነው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)