am_tn/gen/41/27.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዮሴፍ የፈርዖንን ሕልም መተርጐም ይቀጥላል፡፡

የከሱና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች

የቀጨጩና ዐቅሜ ደካማ ላሞች በዘፍጥረት 41:3 የዚህ ተመሳሳይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት የቀጨጩ የእሸት ዛላዎች

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከምሥራቁ ሙቀት አዘል ነፋስ የተነሣ የቀጨጩ ሰባት የእህል ዛላዎች” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ይህን ለፈርዖን የተናገርኩትን … ለፈርዖን ገልጦለታል

ዮሴፍ ፈርዖንን እንደ ሶስተኛ ወገን ሰው ያናግረዋል ይህም አክብሮች መግለጫ መንገድ ነው:: በሁለተኛ ወገን ሰው መልክ ልገለጽ ይችላል:: “እንደተናገርኩህ እነዚህ ይደረጋሉ…… ፈርዖን ለአንተ ገልጦልሃል” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

እይ ሰባት

“እኔ የሚናገረው እውነትና ጠቃሚ ነውና ትኩረት ስጥ፤ ሰባት”

በመላው የግብጸ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ

ጊዜ እንደሚመጣና በወቅቱ በአንድ ቦታ እንደሚሆን ይህ ስለጥጋብ ዓመታት ይናገራል:: አት “የተትረፈረፈ ምግብ በግብጽ በመላው የግብጽ ምድር የሚሆንበት ሰባት ዓመታት ይመጣሉ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)