am_tn/gen/41/22.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ፈርዖን ሕልሙን ለዮሴፍ መናገሩን ቀጠለ

በሕልሜ አየሁ

ይህ ፈርዖን ከነቃና ተመልሶ ከተኛ በኋላ ያየውን ሕልም ይጀምራል፡፡ አት “እንደገናም ሕልም አለምሁ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

እነሆ ሰባት የእሸት ዛላዎች

ስለሚያስገርመው መረጃ ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ፈርዖን “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል::

ሰባት የእሸት ዛላዎች

የእሸት ወይም የእህል የሚለው አባባል የታወቀ ነው:: አት “ሰባት የእህል ዛላዎች” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

በአንድ አገዳ ሲወጡ

“በአንድ አገዳ ሲንዠረግጉ” አገዳ ወፍራምና ረጅም የተክል አካል ነው:: በዘፍጥረት 41:5 ይህን ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

እነሆ ሰባት ሌሎች የእሸት ዛላዎች

ስለሚያስገርመው መረጃ ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ፈርዖን “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል::

የጠወለጉ

የደረቁና ፍሬ አልባ የሆኑ

በምሥራቅ ነፋስ

“ከበረሃማ ቦታ የሚነፍሰው የምሥራቅ ንፋስ” የምሥራቁ ንፋስ ሙቄት አብዛኛውን ጊዜ ለእህሎች እጅግ አደገኛ ነበር::

ተንዠረገገ

አደገ ወይም ፍሬ ሰጠ

የቀጨጩ የእሸት ወይም የእህል ዛላዎች

የእህል የሚለው ቃል የታወቀ ነው በዘፍጥረት 41:7 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ አት የቀጨጩ የእህል ዛላዎች (የተደበቁ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ዋጧቸው

“በሉ” ፈርዖን ያለመው ሕልም ሰው ምግብን እንደሚበላ ጤናማ ያልሆኑ የበቆሎ እህሎች ጤናማ ያልሆኑትን እንደበሉ ነው:: በዘፍጥረት 41:7 የዚህ ተመሣሣይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

የሚችል ማንም አልተገኘም

የሚችል አንድም አልተገኘም ወይም ማንም አልቻለም