am_tn/gen/41/07.md

1.9 KiB

የቀጨጩ የእሸት ወይም የእህል ዛላዎች

እህል የተባለው ቃል የታወቀ ነው:: አት “የቀጨጩ የእህል ዛላዎች” (የተደበቁ ቃላትን የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ዋጡአቸው

በሉአቸው ሰው ምግብን እንደሚበላ የቀጨጩ የእሸት ዛላዎች ጤናማ የእሸት ዛላዎች ሲውጡ ፈርዖን በሕልሙ አየ

ሙሉና ፍሬያቸው የተንዠረገገውን የእሸት ዛላዎች

ጤናማና መልካም የእሸት ዛላዎች

በዘፍጥረት 41:5 የዚህ ተመሣሣይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ ነቃ

ከእንቅልፉ ነቃ

እነሆ

እዚህ እነሆ የሚለው ቃል ፈርዖ ባየው ነገር እንደተገረመ ያሳያል

ሕልም ነበር

ሕልም ሲያልም ነበር

እንዲህም ሆነ

ይህ ሀረግ የተጠቀመው የታሪኩ አድስ ክፍል መጀመሩን ለማመልከት ነው:: በቋንቋዎ ይህን የሚገልጹበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ:: (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይጠቀሙ)

መንፈሱ ታወከበት

እዚህ መንፈሱ የሚለው ቃለ የውስጥ ማንነቱን ወይም ስሜቱን ያመለክታል አት “በውስጥ ማንነቱ ታወከ” ወይም “ታወከ” (ተመሣሣይ ምትክ ቃል ስለመጠቀም ይመልከቱ)

ልኮና አስጠርቶ

አገልጋዮቹን እንደላካቸው መረዳት ይቻላል:: አት “እንዲጠሩ አገልጋዮቹን ላካቸው ወይም አገልጋዮቹ እንደጠሩ አዘዛቸው” (የተደበቁ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

የግብጽ አስማተኞችንና ጥበበኞች

የጥንት ነገሥታት አስማተኞችንና ጥበበኞችን እንደአማካሪዎች ይጠቀሙ ነበር