am_tn/gen/41/04.md

1.7 KiB

የከፉና የከሱ

“ደካማና የከሱ” በዘፍጥረት 41:3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

መልካምና የወፈሩ

“ጤናማና የደለቡ ወይም በደንብ የበሉ” በዘፍጥረት 41:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

ነቃ

ከእንቅልፉ ነቃ

ሁለተኛ ጊዜ

“ሁለት” የሚለው ቃል ተራ ቁጥር ሁለት ነው:: አት “እንደገና” (ተራ ቁጥሮችን ይመልከቱ)

እነሆ ዛላዎች

እዚህ እነሆ የሚለው ቃል ፈርዖን ባየው ነገር እንደተገረመ የሚያሳይ ነው

የእሸት ዛላዎች

ዛላዎች ፍሬዎች የሚንዠረግጉበት የበቆሎ ተክል አካል ነው

በአንድ የእህል አገዳ ላይ

“በአንድ አገዳ ላይ ያፌራውን ወይም የተንዠረገገውን” አገዳ ወፍራምና ረጅም የተክል ክፍል ነው::

በአንዱ አገዳ ላይ የተንዠረገገና ያማረ

በአንድ አገዳ ጤናማና ያማረ

የቀጨጩና በምሥራቅ ንፋስ የተመቱ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ያም ከምሥራቅ ደረቅ አየር የትነሳ የቀጨጩና በዋግ የተመቱ” (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

የምሥራቅ ንፋስ

የምሥራቅ ንፋስ ከረሃማ ተነሥቶ የሚነፍስ ነው፡፡ የምስራቅ ንፋስ ሙቀት እጅግ ጐጂ ነው፡፡

ዛላዎች ወጡ

ዛላዎች አደጉ ወይም ተንዠረገጉ