am_tn/gen/40/01.md

1.5 KiB

ከዚህም በኋላ

ይህ ሀረግ የተጠቀመው በታሪኩ አዲስ ክስተት መጀመሩን ለማመልከት ነው፡፡ (አዲስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)

የመጠጥ አሳላፊ

ይህ ለንጉሡ መጠጥ የሚያቀርብ ሰው ነው

እንጀራ ቤቱ

ይህ ለንጉሡ ምግብ የሚያዘጋጅ ሰው ነው

ጌታቸውን በደሉት

ጌታቸውን አስቆጡት

የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ

ዋና የመጠጥ አሳላፊና ዋና እንጀራ እቅራቢ

በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው እስር ቤት አስገባቸው

በዘበኞቹ አለቃ በሚተዳደረው የቤት ውስጥ እስር ቤት አስገባቸው

አስገባቸው

ንጉሡ ወደ እሥር ቤት አላስገባቸውም ነገር ግን እንዲታሠሩ አዘዛቸው፡፡ አት “እነርሱ እንዲያስገቡ አደረጋቸው” ወይም “ዘበኛው እንዲያስገባቸው አዘዘ” (ተዛማጅ ምትክ አባባሎችን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ዮሴፍ ወደጋዘበት እስር ቤት

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ይህ ዮሴፍ የነበረበት ተመሣሣይ እስር ቤት ነው ወይም ይህ ጲጥፋራ ዮሴፍን ያስገባበት ተመሣሣይ እስር ቤት ነው (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)