am_tn/gen/39/07.md

2.1 KiB

ከዚህ በኋላ እንደዚህ ሆነ

እናም ደግሞ ይህ ሀረግ አድስ ክስተት መጀመሩን ሊያመለክት ተጠቅሞአል (አዲስ ክስተት ማታወቅ ይመልከቱ)

እይው

ስሚው ዮሴፍ የጲጥፋራን ሚስት መስብ/ትኩረት ለማግኘት ይህን ቃል ተጠቅሞአል

ጌታዬ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም

“ጌታዬ በኃላፊነቴ ሥር ስላለው ስለቤቱ ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም”:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ጌታዬ ስለቤቱ ያምነኛል” (ድርብ አሉታዊነት ይመልከቱ)

ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኃላፊነት ለእኔ ስለሰጠኝ

አንድ ነገር “በአንድ ሰው ኃላፊነት ሥር” ሲሆን ያ ሰው እንዲንከባከበውና እንዲጠብቀው ኃላፊነት አለው ማለት ነው:: አት፡ “ያለውን ሁሉ በኃላፊነት ስለሰጠኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም

እዚህ ጸሓፊው ኃላፊነትን እንደ ትልቅነት ይናገራል አት: “ከማንም ሰው የበለጠ ለዚህ ቤት ኃላፊነት አለኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ከአንቺ በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም

ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እርሱ ያለሰጠኝ ነገር ቢኖር አንቺን ብቻ ነው” (አሉታዊነትን በአዎንታዊነት የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

እንዴት ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ

ዮሴፍ ትኩረት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማል ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አልሠራም (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)