am_tn/gen/39/05.md

3.2 KiB

ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር የግብጻዊውን ቤት ባረከ

ተውላጤ ስሞችን ከመጠቀምዎ በፊት “ዮሴፍ” እና “ግብጻዊው” የሚሉ ቃላትን መጠቀም ይችላሉ:: ግብጻዊው ዮሴፍን በቤቱና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ኃላፊነት ሰጠው እናም ከጊዜ ወደ ጊዜ በዮሴፍ ምክንያት እግዚአብሔር የግብጻዊውን ቤት ባረከ::

እንዲህም ሆነ

እነዚህ ሁለቱ ጥቅሶች ለሚቀጥለው ክስተት ዳራ መረጃ እንደሆኑ ለአንባቢያን ለመናገር ይህ ሀረግ ተጠቅሞአል

እርሱም እርሱን በቤቱና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ሾመው

ጲጥፋራ ዮሴፍን በቤቱና ባለው ተብት ሁሉ ላይ ሾመው

ባረከው

በሚባረከው ነገር ወይም ሰው መልካም ወይም ጠቃሚ ነገር እንዲደረግ ምክንያት መሆን ማለት ነው

የእግዚአብሔር በረከት ሆነ

እዚህ ጸሐፊው እግዚአብሔር የሰጠውን በረከት በአንድ ነገር ላይ እንደተቀመጠ መሸፈኛ አድርጐ ይናገራል:: አት: “እግዚአብሔር ባረከ” ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ

በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ

ይህ ቤት እረሻውንና ከብቶችን ያለመክታል የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “በጲጥፋራ ቤትና በከብቶችና እርሻው ሁሉ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቀ መረጃ ይመልከቱ)

ጲጥፋራ ማንኛውንም ጉዳይ በዮሴፍ ቁጥጥር ሥር አድርጐ/በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር

አንድ ነገር በአንድ ሰው ቁጥጥር ሥር ሲሆን ያ ሰው ሊጠብቀውና ሊንከባከበው ኃላፊነት አለው ማለት ነው አት: “ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ለዮሴፍ ስልጣን ሰጠው”

ከሚበላው እንጀራ በቀም ምንም የሚያውቀው አልነበረም

ምን ምግብ መመገብ እንዳለበት ከመወሰን በቀር በቤቱ ስላለው ማንኛውም ነገር አይጨነቅም ነበር ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል አት ጲጥፋራ ምን መመገብ እንደሚፈልግ ብቻ ማሰብ ነበረበት በቤቱ ስላለው ማንኛውም ነገር መጨነቅ የለበትም (ግምታዊ እውቀትና ጥልቀ መረጃ ይመልከቱ)

አሁንም

“አሁንም” የሚለው ቃል ስለ ዮሴፍ ዳራ መረጃ ለመስጠት በታሪኩ መስመር ውስጥ ጣልቃ ማስገባቱን ያመለክታል (ዳራ መረጃ ይመልከቱ)

ዮሴፍ መልከ መልካምና ውብ ነበር

ሁለቱም ቃላት ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ዮሴፍ የሚያስደስት ቁመና እንዳለው ያመለክታሉ:: ጠንካራና ጥሩ ቁመና ነበረው:: አት: “ጠንካራና መልከመልካም ነበር”