am_tn/gen/37/34.md

1.5 KiB

ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ

ይህ ጥልቅ መጨነቅንና ሀዘንን የሚያመለክት ነው ይህ በግልጽ ሊገለጽ ይችላል አት ያዕቆብ እጅግ ስላዘነ ልብሱን ቀደደ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

በወገቡም ማቅ ታጥቆ

ወገብ የሰውነት መሀከለኛው አካል ነው አት ማቅ ለብሶ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ተነሡ

እዚህ አባታቸውን ለማጽናናት የልጆች መጥጣት እንደ መነሣት ተደርጐ ተገልጾአል:: አት: “ወደ እርሱ መጡ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እርሱ ግን ሊጽናና ባለመቻሉ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ነገር ግን እንዲያጽናኑት አልፈቀደም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ወደ ሙታን ሥፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ

ከዛሬ ጀምሮ እስከሚሞት ድረስ እንደሚያዝን ይገልጻል:: አት: “በሚሞትበትና ወደ ሙትን ሥፍራ በሚወርድበትም ጊዜም በእርግጥ እያዘንኩ ይሆናል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ምድያማዊያን ሸጡት

ምድያማዊያን ዮሴፍን ሸጡት

ለዘበኞች አለቃ

ንጉሡን ለሚጠብቁ ዘበኞች መሪ