am_tn/gen/37/18.md

1014 B

በሩቅ አዩት

በሩቅ እያለ የዮሴፍ ወንድሞች አዩት

ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ

እርሱን ለመግደል አቀዱ

ያ ሕልም ዐላሚ መጣ

ያ ባለ ሕልም ይሄው መጣ

ስለዚህ አሁንም ኑ

ይህ አባባል ወንድሞቹ ዕቅዳቸውን መተግበር መጀመራቸውን ያሳያል:: አት: (ስለዚህ አሁን ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ክፉ አውሬ

አደገኛ አውሬ ወይም ሰው ጨካኝ አውሬ

ቦጫጭቆ በላው

ንጥቆ በላው

ከሕልሞቹም የሚሆነውን እናያለን

ወንድሞቹ ሊገድሉት አቅደዋልና ስለዚህ እስከሞተ ድረስ ሕልሞቹ ይፈጸሙ እንደሆን መናገራቸው አሽሙራዊ/ሽሙጣዊ አባባል ነው:: አት “እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን” (በአሽሙር/ሽሙጥ መንገድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)