am_tn/gen/37/07.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ስለሕልሙ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ይናገራል

እነሆ

“እነሆ” የሚለው ቃል ለሚቀጥለው አስደናቂ ሃሳብ ትኩረት እንዲሰጠው ያነቃል

እኛ ሁላችን

“እኛ” የሚለው ቃል ዮሴፍና ወንድሞቹን ሁሉ ያጠቃልላል (ሁሉን ያቀፈ እኛ ይመልከቱ)

ነዶ እናሥር ነበር

እህል ከታጨደ በኋላ ፍሬው ከገለባው እስኪበጠር ድረስ በየነዶው ታሥሮና ተከምሮ ይጠበቃል

እንሆ

“እነሆ” የሚለው ቃል ዮሴፍ ባየው እንደተደነቀ ይገልጻል

የእኔ ነዶ በድንገት ተነሥታ ቀጥ ብላ ቆመች የእናንተ ነዶዎች ዙሪያዋን ከበው ለእኔ ነዶ ሰገዱላት

እዚህ እንደሰው ነዶዎች ሲቆሙና ሲሰግዱ ይታያል እነዚህ ነዶዎች ዮሴፍንና ወንድምቹን ይወክላሉ (በሰውኛ መንገድ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

በላያችን ልትነግሥብን ይሆን? ልትገዛ ይሆን?

እነዚህ ሁለቱም ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው የዮሴፍ ወንድሞች ጥያቄዎችን በመጠቀም ዮሴፍን ማላገድ ጀመሩ እነዚህ በዐረፍተ ነገሮች መልክ ሊገለጹ ይችላሉ አት ንጉሣችን አትሆንም እኛም ለአንተ አንሠግድም (አግናኝ ጥያቄዎችንና ተዛማጅ ተመሣሣይ አባባል ይመልከቱ)

እኛን ልትገዛ

እኛ የሚለው ቃል ዮሴፍን ሳይሆን ወንድሞቹን ያመለክታል (ሁሉን አቀፍና ሁሉን የማያቅፍ “እኛ” ይመልከቱ)

ለሕልሙና ለተናገረው ቃል

ስለ ሕልሙና ልሰተናገረው ቃል