am_tn/gen/35/04.md

2.1 KiB
Raw Permalink Blame History

ስለዚህ ሰጡት

“ሁሉም የያዕቆብ ቤት ሰጠ” ወይም “የያዕቆብ ቤተሰብና አገልጋዮቻቸው ሰጡት”

በእጃቸው ያሉትን

እዚህ “በእጃቸው ያሉት” የእነርሱ የሆኑትን ይወክላል:: አት: “ሀብታቸው የሆኑትን ወይም ያላቸውን” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

የጆሮ ጉትቾቻቸውን

ጉትቾቻቸውን ተገቢ ትርጉሞች እነሆ 1 የጆሮቻቸውን ወርቅ ብዙ ጣዖታትን ሊሠሩ ሊጠቀሙ ይችላሉ 2 እነዚህ ጉትቾች የሴኬም ከተማ ሰዎችን በተዋጉና ሁሉን ሰዎች በገደሉ ጊዜ የበዘበዙአቸው ናቸው:: ጉትቾች ስለኃጢአታቸው የሚያውሱ ይሆናሉና::

በዙሪያው ባሉ ከተሞች ሁሉ እግዚአብሔር ድንጋጤ ለቀቀባቸው

ያዕቆብንና ቤተሰቡን የከተሞች ሰዎች እንዲደነግጡ እግዚአብሔር ያደረገው ድንጋጤ እንደ አንድ ነገር በከተሞች እንደወደቀ ተደርጐ ተገልጾአል:: “ድንጋጤ” የተባለው ረቂቅ ስም እንደ “ፍርሃት” ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር በዙሪያው ያሉ የከተሞች ሰዎች ያዕቆብንና በቤተሰቡን እንዲፈሩ አደረገ” ዘይቤያዊ አነጋገርና ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ

በከተሞች ላይ

“ከተሞች” በከተሞች የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላሉ::

የያዕቆብ ወንዶች ልጆች

ከያዕቆብ ቤተሰብ ማንም እንዳልተጠቃ ይገልጻል ነገር ግን የያዕቆብ ሴት ልጅ ከተደፈረች በኋላ ስምዖንና ሌዊ የሴኬምን ከነዓናዊያን ዘመዶችን አጠቁአቸው በዘፍረት 34:3 ያዕቆብ ሊበቀሉ ይፈልጉ ይሆናል ብሎ ፈርቶአል አት የያዕቆብ ቤት ወይም የያዕቆብ ቤተሰብ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)