am_tn/gen/35/01.md

1.2 KiB

ወደ ቤተል ውጣ

ውጣ የሚለው ቃል የተጠቀመው ቤቴል ከሴኬም በከፍታ ላይ ስለሚገኝ ነው

በዚያ መሠዊያ ሥራ

እግዚአብሔር ስለራሱ በሶስተኛ ሰው መንገድ ይናገራል:: አት: “ለእኔ ለአምላክህ መሠዊያ ሥራ” (እንደ አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው መግለጽን ይመልከቱ)

ለቤቱ ሰዎች እንዲህ አላቸው

ለቤተሰቡ እንዲህ አላቸው

በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልእክት አስወግዱ

“ጣዖታትን አስወግዱ” ወይም “ሐሰተኞች አማልእክትን አስወግዱ”

ራሳችሁን አንጹ ልብሳችሁን ለውጡ

ይህ እግዚአብሔርን ለማምለክ ከመቅረብ በፊት በአካላዊና ሥነምግባራዊ ሕይወት ራስን የማንጻት ልምድ ነበር

ልብሳችሁን ለውጡ

አድስ ልብሶችን መልበስ ወደ እግዚአብሔር ከመቀረባቸው በፊት ራሳቸውን ንጹህ የማድረጋቸው ምልክት ነበር (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

በመከራዬ ቀን

በመከራዬ ጊዜ ወይም በጭንቀተ ጊዜ