am_tn/gen/34/30.md

2.3 KiB

አስጨነቃችሁኝ

ለአንድ ሰው የጭንቀት ምክንያት መሆን ጭንቀት በአንድ ሰው ላይ እንደሚመጣና እንደሚቀመጥ ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል አት: “ትልቅ ችግሮችን ፈጥራችሁብኛል” (ዜይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ)

በዚህ አገር በሚኖሩ ዘንድ እንደጥንብ አስቆጠራችሁኝ

ያዕቆብ በዙሪያው በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ እንዲጠላ ማድረግ የያዕቆብ ልጆች እርሱን እንደ መጥፎ ሽታ እንዳደረጉ ተገልጾአል ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “በምድሪቱ በሚኖሩ ዘንድ የተጠላሁ እንዲሆን አድርጋችሁኛል” (ዜይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ)

እኔ በቁጥር አነስተኞች ነኝ ቢያጠቁኝ እኔንና ቤተሰቤን ያጠፋሉ

እዚህ “እኔ” እና “እኔን” የሚሉ ቃላት ያዕቆብን ቤተሰብ በአጠቃላይ ይወክላሉ:: ያዕቆብ የቤተሰቡ መሪ ከመሆኑ የተነሳ “እኔ” ወይም “እኔን” ይጠቀማል:: አት: “ቤተሰብ አነስተኛ ነው … ተባብረው ቢነሡብኝና ቢያጠቁኝ ሁላችንንም ያጠፋሉ::” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ተባብረ ይነሡና ያጠቁኛል

ሠራዊት ይፈጥሩና ያጠቁኛል ወይም ሠራዊት ይፈጥሩና ያጠቁናል

እኔም እጠፋለሁ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ያጠፉኛል ወይም ያጠፉናል ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ”

ሴኬም በሴተኛ አዳሪ/በጋለሞታ እንደሚደረግ በእኀታችን ያደርግባትን?

ሴኬም ያደረገው ጥፋትና ሞት እንደሚገባው አበክረው ለመግለጽ ሌዊና ስምዖን ጥያቄ ይጠቀማሉ:: አት: “ሴኬም እህታችንን እንደ ሴተኛ አዳሪ/ጋለሞታ አድርጐ ባልቆጠረ ነበር!” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)