am_tn/gen/34/11.md

1.6 KiB

ሴኬም ደግሞ አባትዋን እንዲህ አለ

ሴኬም የዲናን አባት ያዕቆብን እንዲህ አለ

በእናንት ፊት ሞገስ ላግኝ እንጂ የጠየቅሁትን ሁሉ እሰጣለሁ

“ሞገስ ማግኘት” የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ማረጋገጥ የሚናገር ዘይቤያዊ አነጋገር ነው ደግሞም ዓይኖች ማየትን ሲወክሉ ማየት ሀሳብን ወይም ፍረጃን ያመለክታሉ:: አት: “እንደተቀበላችሁን ካረጋገጥሁ የሚትጠይቁኝን ሁሉ እሰጣለሁ”:: (ፈሊጣዊና ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ጥሎሽ

በአንዳንድ ባህሎች በጋብቻ ጊዜ ለሙሽሪቱ ቤተሰብ ሙሽራው በገንዘብ በንብረት በእንስሳትና በሌላም መልክ ስጦታ መስጠት የተለመደ ነው

የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም ለሴኬምና ለኤሞር የሚያታልል መልስ ሰጡ

ማታለል የሚለው ረቂቅ ስም መዋሽት እንደሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: ነገር ግን የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ለሴኬምና ለኤሞር በመለሱአቸው ጊዜ ዋሹአቸው (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)

ሴኬም ዲናን አስነውሮአታል

ከእርሱ ጋር እንዲትተኛ በመድፈሩ ሴኬም ዲናን እጅግ በጣም አዋርዶአታል አስነውሮአታል ማለት ነው:: በዘፍጥረት 34:5 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::