1.1 KiB
1.1 KiB
ኤሞር ያዕቆብን ሊያነጋግረው ወጣ
ኤሞር ያዕቆብን ሊያነግረው ሄደ
የያዕቆብ ወንዶች ልጆች አዘኑ
ወንዶች ልጆች እጅግም ተቆጡ ወይም ደነገጡ
እስራኤልን አስነወረ
እዚህ እስራኤል የሚለው ቃል እያንዳንዱን የእስራኤል ቤተሰብ አባል ያመለክታል እስራኤል እንደብሔር ተደፍሮአል:: አት: “የእስራኤልን ቤት አዋርዶአል” ወይም “የእስራኤልን ስዎች አሳፍሮአል” (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘጥቤ ይመልከቱ)
የያዕቆብን ሴት ልጅ ስለደፈረ
የያዕቆብን ልጅ ስለደፈራት
ይህ ዓይነት ተግባር መደረግ አይገባውም
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እንደዚህ አስነዋሪ ነገር ማድረግ አይገባውም ነበር” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)