am_tn/gen/31/36.md

1.5 KiB

እርሱም እንዲህ አለው

ያዕቆብ ላባንን እንዲህ አለ

ወንጄሌ ምንድነው? ይህን ያህል የምታሳድደኝ ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው?

ወንጄሌ ምንድነው እና ኃጢአቴ ምን ሆን የሚሉ ሀረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ያዕቆብ ላባንን ምን ስህተት እንደሠራ ይጠይቀዋል አት ይህን ያህል በጽኑ የምታሳድደኝ ምን ስህተት ቢፈጽም ነው? (ተጓዳኝ ተነጻጻሪ አባባል ይመልከቱ)

በጽኑ

እዚህ “ጽኑ” የሚለው ቃል ላባን በማጣደፍ ያዕቆብን ለመያዝ ባለው ተነሣሽነት እንዳሳደደው ይገልጻል (ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ)

ከቤትህስ ዕቃ ሁሉ ምን አገኘህ?

ያንተ ሆኖ ያገኘሄው ዕቃ የትኛው ነው?

በእኛ ዘመዶች ፊት አቅርብ

እዚህ እኛ የሚለውቃል የያዕቆብ ዘመዶችና የላባንን ዘመዶች ያመለክታል:: አት: ያገኘሄውን ማንኛውንም ነገር በዘመዶቻችን ፊተ አቅርብ (አካታች አንደኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)

እነርሱ ሁለታችንን ይፍረዱ ወይም እነርሱ ይፍረዱን

እዚህ “ሁለታችን” ያዕቆብንና ላባን ያመለክታል:: “ይፍረዱን” የሚለው አባባል ከክርክሩ የትኛው ትክክል እንደሆነ ይወስኑ ማለት ነው፡፡