am_tn/gen/31/31.md

1.2 KiB

ልጆችህን ከእኔ የምትቀማ ስለመሰለኝና ስለፈራሁ በድብቅ ወጣሁ፡፡

በድብቅ የወጣሁት ልጆችህን ከእኔ ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ ብዬ ስለፈራሁ ነው፡፡

ከእኛ መካከል የአንተን የጣዖታት ምስል ደብቆ የተገኘ ሰው ካለ ይሙት

ይህ በአዎንታዊ መንገድ መገለጽ ይችላል አት ጣዖቶችህን የሰረቀ ማንም ቢገኝ እንገድላለን (ምጸት ይመልከቱ)

ዘመዶቻችን/የእኛ ዘመዶች ባሉበት

የእኛ የሚለው ቃል የያዕቆብ ዘመዶችንና የላባን ዘመዶች ያመለክታል:: ሁሉም ዘመዶች ፍትሃዊና ግልጽ መሆኑን ለማረጋገጥ ያዩታል (ሁሉ አቀፍ አንደኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)

ያንተ የሆነ አንዳች ነገር ከኔ ዘንድ ቢገኝ ውሰድ

በእኛ ዘንድ ካለው ያንተ የሆነውን ፈልግና ውሰድ

ያዕቆብ ራሔል እነዚያን/ጣዖታቱን መስረቋን አያውቅም ነበር

ይህም ታሪኩን ወደ ያዕቆብ ሕይወት ዳራ መረጃ ይቀይራል (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)