1.2 KiB
1.2 KiB
እናንተን ልጐዳችሁ ነበር
እዚህ “እናንተ” ብዙና ከያዕቆብ ጋር ያሉትን ሁሉ ያመለክታል:: አት: “ሊጐዳችሁ የሚያስችለኝ ከእኔ ጋር ብዙ ሰዎች ነበሩ” (የሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ አለኝ
“ክፉ ሆነ ደግ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመው “ምንም” ለማለት ነው፡፡ በዘፍጥረት 31:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት፡ “ያዕቆብን ከመሄድ ለማቋረጥ ለመሞከር ምንም ነገር እንዳትናገር” (See: Merism)
አንተም ሄደሃል
አንተ የሚለው ነጠላና ያዕቆብን ያመለክታል:: (የሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ወደ አባትህም ቤት
እዚህ ቤት ቤተሰብን ይወክላል:: አት: “ወደ አባትህና ሌሎች ቤተሰብህ ቤት ለመመለስ” (ክፍልን ሙሉና ሙሉውን ክፍል አድርጐ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
አምላኮቼን
ጣዖቶቼን