am_tn/gen/31/26.md

1.8 KiB

ልጆቼን የጦር ምርኮኛ ይመስል አካልበህ ወሰድናቸው

ያዕቆብ ቤተሰቡን ከራሱ ጋር ወደ ከነዓን ምድር መውሰዱ ልክ ያዕቆብ እንደ የጦር ምርኮኞችን እናም አሰገድዶአቸው እየወሰደ እንዳለ ላባን ይናገራል ላባን ስለተቆጣና ያዕቆብ ስላደረገው ነገር ጸጸት እንዲሰማው አግንኖ ይናገራል:: (ተመሣሣይ ንጽጽር የማጋነንና ገሃዳዊ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ተደብቀህ ሄድህ

በድብቅ ሸሸህ

ፍስሐ በማድረግ

በደስታ

በከበሮ/ ታምቡርና በበገና

እነዚህ መሣሪያዎች ሙዝቃን የሚገልጹ ናቸው፡፡ አት፡ “እናም በሙዝቃ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ታምቡር

የከበሮ ዓይነት ለምት የሚሆን አናት ያለው ዙሪያሙ ከብረት የተሠራና መሣሪያው በሚመታበት ጊዜ የሚርገበገብ የሙዝቃ መሣሪያ ነው ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ

ወንዶች የልጅ ልጆቼን እንዲስማቸው

እዚህ ወንዶች የልጅ ልጆች ወንድ ሆነ ሴት ሁሉን የልጅ ልጆችን ይወክላሉ:: አት: “የልጅ ልጆቼን እንዲስማቸው” (በወንዴ ጾታ የተጠቀሱ ሴት ጾታንም የመግለጽ አባባል ይመልከቱ)

አሁን የሠራሄው የጅል ሥራ ነው

በጅልነት አድርገሄዋል

አሁንም

ይህ የዚያን ጊዜ ማለተ አይደለም ነገር ግን ለሚከተለውን ጠቃሚ ነገር ትኩረት እንደሰጥበት ነው