am_tn/gen/29/31.md

1.6 KiB

ልያ አልተወደደችም

ይህ ተሻሪ ግሥ በያዘ መልክ ወይም በገቢር ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ያዕቆብ ልያን አልወደዳትም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

እንዳልተወደደች

ያዕቆብ ራሔልን ከልያ ይልቅ እንደወደዳት በማተኮር አግንኖ የሚናገር ነው አት ከራሔል አሳንሶ ወደዳት (አግንኖና በገሃድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ማሕጸንዋን ከፈተላት

እግዚአብሔር ልያ እንዲትጸንስ ማድረጉ እግዚአብሔር ማሕጸንዋን እንደከፈተ ተደርጐ ተነግሮአል:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

መካን ነበረች

ሊትጸንስ አልቻለችም

ልያ ጸነሰች ልጅም ወለደች

ልያ ጸነሰች ወንድ ልጅም ወለደች

ስሙን ሮበል አለችው

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: ሮበል የሚለው ስም ‘ወንድ ልጅ አየሁ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

እግዚአብሔር መከራዬን ስለተመለከተልኝ

ልያ ያዕቆብ ስላልተቀበላት በስሜታዊ ሕመም ነበራት:: “መከራ” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር እንደተሰቃየሁ አየኝ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)