am_tn/gen/29/23.md

1.6 KiB

አብሮአት ተኛ

ይህ የሚገልጸው ምሽት ስለነበረና ስላላያት ከልያ ጋር መሆኑን ያዕቆብ አላወቀም ነበር:: የዐረፍተ ነገሩ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ላባን ዘለፋ የተባለች አገልጋዩን ለልጁ ለልያ ደንገጡር እንድትሆን ሰጣት

እዚህ ጸሐፊው ላባን ዘለፋን ለልያ እንደሰጠ መረጃ ይሰጣል፡፡ ዘለፋን ለልያ ከሠርግ በፊት ሳይሰጣት አይቀርም:: (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ይመልከቱ)

እነሆ ልያ ሆና ተገኘች

ያዕቆብም ልያ በአልጋ አብሮአት በማየቱ ተገረመ:: “እነሆ” የሚለው ቃል ያዕቆብ ባየው ነገር እንዴት እንደተደነቀ የሚያሳይ ነው፡፡

ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ?

ያዕቆብ ቁጣውንና መገረሙን ለመግለጽ ጥያቄ ይጠቀማል ይህ ቅኔ አዘልጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡ “ይህን ለእኔ ታደርጋለና ብዬ አላምንህም” (See: RhetoricalQuestion)

ያገለገልሁህ ለራሔል ብዬ አልነበረምን?

ያዕቆብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠቀመው ላባን ያታለለውን ጉዳቱን ለመግለጽ ነው ይህ ቅኔ አዘል ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገልግየሃለሁ (See: Rhetorical Question)