am_tn/gen/29/01.md

985 B

የምሥራቅ ሰዎች

ከከነዓን ምድር በስተምሥራቅ የሚገኙ የጳዳን አራም ሰዎች ማለት ነው::

እነሆ በአንድ ሜዳ ላይ ሶስት የበግ መንጋዎች ተኝተው በነበሩበት

እነሆ የሚለው ቃል በትልቁ ታሪክ ውስጥ አንድ ሌላ ክስተት መጀመሩን ያመለክታል:: በሚትተረጉሙበት ቋንቋ ይህን የመግለጽ መንገድ ሊኖሮት ይችላል::

ከዚያ ጉድጓድ

ከዚሁ ጉድጓድ ይህ ሀረግ ታሪኩን ወደ ዳራው መረጃ ይመልስና እንዴት እረኞች በጐችን ውሃ እንደሚያጠጡ ይናገራል

እነርሱ ውሃ ያጠጣሉ

“እረኞች ውሃ ያጠጣሉ” ወይም “በጐችን የሚጠብቁ ውሃ ያጠጣሉ”

የጉድጓዱ አፍ

አፍ ጉድጓዱ የተከፈተበትን ቦታ ያሳያል:: አት: “ጉድጓዱ የተከፈተበት ቦታ”