am_tn/gen/28/20.md

1.2 KiB

ስእለት ተሳለ

“ስእለት አደረገ” ወይም “በተለይ ለእግዚአብሔር ቃል ገባ”

እግዚአብሔር እንዲህ…. እግዚአብሔር አምላኬ ይሆናል

ያዕቆብ እግዚአብሔርን በሶስተኛ ሰው አገላለጽ ያናግረዋል ይህ በሁለተኛ ሰው አገላለጽ ሊገለጽ ይችላል:: አት: አንተ እንዲህ…የማመልከው አምላኬ ትሆናለህ” (ተዛማጅና ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

የሚበላውን እንጀራ ቢትሰጠኝ

እዚህ “እንጀራ” አጠቃላይ ምግብ ይገልጻል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ወደ አባቴ ቤት

“ቤት” ለያዕቆብ ቤተሰብን ይገልጻል አት ወደ አባቴና ወደሌሎች የቤተሰብ አባላት (ተዛማጅና ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

የተቀደሰ ድንጋይ

ድንጋዩ እግዚአብሔር የተገለጠበትን ቦታ ያመለክታልና ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት ቦታ ይሆናል