am_tn/gen/28/03.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይስሐቅ ለያዕቆብ መናገሩን ቀጠለ

ልጆች አፍራ ዘርህን ያብዛው

ያብዛው የሚለው ቃል እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዴት ፍሬያማ እንደሚያደርገው ይገልጻል:: አት: “ብዙ ልጆችንና ትውልድ ይሰጥሃል” (ድርብ ቃላት ይመልከቱ)

ለአብርሃም የሰጠውን በረከት ለአንተና ለዘሪህ ይስጥ

ይህ የሚናገረው አንድን ሰው ስለመባረክ ሲሆን በረከት አንድ ሰው ሊሰጥ እንደሚችል ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል ረቂቅ ስም “በረከት” “ይባርክ” በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት: “አብርሃምን እንደባረከ አንተንና ዘርህን እግዚአብሔር ይባርክ” ወይም “ለአብርሃም የገባውን ተስፋ ለአንተና ለዘርህ እግዚአብሔር ይስጥ”:: (ዜይቤያዊ አነጋገርና ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

ምድሪቱን ያወርስህ ዘንድ

እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር ለያዕቆብና ለዘሩ መስጠቱ ልጅ ከአባቱ ገንዘብ ወይም ሀብት እንደሚወርስ ተደርጐ ተገልጾአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

የሚትኖርበትን ይህችን ምድር

“እስከአሁን ያለህበትን ምድር”

እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠውን

እግዚአብሔር ለአብርሃም ተሰፋ የሰጠውን