am_tn/gen/27/39.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

እርሱን አለው

ዔሣውን አለው

ቦታውን ተመልከት

ትኩረት አድርግ ስለቦታው የሚናገረው እውነትና ጠቃሚ ነው

ከምድር በረከት የራቀ

ይህ ስለምድር ለምነት የሚናገር ምሳለያዊ አነጋገር ነው አት ለም ያልሆነ መሬት

ለአንተ…. አንተ

በ27:39-4 እነዚህ ተውላጤ ስሞች ነጠላና ዔሣውን ያመለክታሉ:: ነገር ግን ይስሐቅ የሚናገረው ለዔሣው ትውልድም የሚሆን ነው:: ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ::

ከላይም ከሰማይ ጠል

ጠል በሌሊት በተክሎች ላይ የሚሆን የውሃ ጠብታ ነው:: በትርጉም ይህን ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ተክሎችዎን ለማጠጣት የሌሊት ጠል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

በሰይፍ ትኖራለህ

ሰይፍ ለአመጽ የሚቆም ነው:: አት: “ለመኖር የሚያስፈልግህን ለማግኘት ሰዎችን ትዘርፋለህ ትገድላለህ” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል ስለመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ቀንበሩ ከጫንቃህ ላይ ወዲያው ትጥላለህ

ይህ አንድ ጌታ እንዳለውና የጌታውም የበላይ አገዛዝ አንደሚሸከምበት ቀንበር እንደተጫነበት ተደርጐ ተነግሮአል አት ከግዛቱ ራስህን ነጻ ታወጣለህ:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)