1.1 KiB
1.1 KiB
ልጄ ሆይ ማንኛውም ርግማን በእኔ ላይ ይድረስ
“ልጄ ሆይ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን” መረገም ርግማን በአንድ ሰው ጫንቃ ላይ እንደሚሆን ዕቃ ተደርጐ ተገለጾአል:: አት “ልጄ ሆይ አባትህ አንተን ከመርገም እኔን ይርገመኝ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ድምጼን ታዘዝ
ርብቃ “ድምጼን” ያለችው የምትናገረውን ነገር ለማመልከት ነው:: አት: “የሚናገርህን ታዘዝ” ወይም “ታዘዘኝ” (ተዛማጅ ባሕሪይ የሚገልጽ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
እነርሱን አምጣልኝ
“ጠቦቶቹን አምጣልኝ”
ልክ አባቱ እንደሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ አዘጋጀችለት::
ጣፋጭ የሚለው ቃል በጣም ጥሩ ጣዕም ያለውን ነገር ያመለክታል:: በዘፍጥረት 27:4 ተመሳሳይ ቃል እንዴት እንደተተረጐመ ይመልከቱ::