am_tn/gen/27/05.md

2.4 KiB

“በወቅቱ”

በወቅቱ የሚለው ቃል ትኩረቱ ወደ ርብቃና ያዕቆብ መዞሩን ያሳያል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ርብቃም ይስሐቅ ለልጁ ለዔሣው ሲነግር ትሰማ ነበር

“ይስሐቅ ለልጁ የተናገረውን ርብቃ ትሰማ ነበር”

ዔሣው … ለማምጣት ሄደ:: ርብቃም ያዕቆብን እንዲህ አለችው

ዔሣው ከወጣ በኋላ ርብቃ የሰማችውን ለያዕቆብ ተናገረች:: አት: “ዔሣው ለማምጣት በወጣ ጊዜ ርብቃም ለያዕቆብ ተናገረች” (አያየዥ ቃላት ይመልከቱ)

ለዔሣው ለልጁ …. ለያዕቆብ ልጅዋን

ዔሣውና ያዕቆብ ሁለቱም የይስሐቅና የርብቃ ልጆች ናቸው አንድ ወላጅ አንዱን ልጅ ከሌላኛው ልጅ አብልጦ እንደሚወድ ተደርገው የእርሱ ልጅ እና የእርስዋ ልጅ ተብለው ተጠርተዋል::

ይሄው ተመልከት

“ይኼው ተመልከት” የሚለው ሀረግ ለሚቀጥለው ሃሳብ አጽንዖት የሚሰጥ ነው:: አት: “በጥሞና ስማ ግምታዊ እውቀት” ወይም “ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ”

እርሱም አለ ከመሞቴ በፊት በእግዚአብሔር ፊት እንዲመርቅህ ጥሩ ጣዕም ያለው ምግብ እንድበላ አዘጅልኝ

ይህ በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ ነው:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል አት: “ለዔሣውም ነገረው; ‘የዱር እንስሳ እንዲያድንና የሚወደውን ጣዕም የሥጋ ምግብ እንዲያዘጋጅለት’ ከዚያም ከመሞቱ በፊት በእግዚአብሔር ፊት የስሐቅ ዔሣውን እንዲባርከው” (በጥቅስ ውስጥ ጥቅሶችንና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)::

አድነህም አምጣልኝ

“የዱር እንስሳት አድነህ ገድለህ አምጣልኝ”

የምወደው ዓይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ

“የምወደው ዓይነት የሥጋ ምግብ አዘጋጅልኝ” ይህን በዘፍጥረት 27:4 እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

በእግዚአብሔር መገኘት እንዲመርቅህ

“በእግዚአብሔር ፊት እንዲመርቅህ”