am_tn/ezr/08/21.md

2.1 KiB
Raw Permalink Blame History

የአኅዋ ሸለቆ

ይህ አኅዋ ተብሎ ወደ ሚጠራው ወንዝ የሚፈስሰው የሸለቆ ስም ነው፡፡ አኅዋነና ሸለቆውን በዕዝራ8፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት

ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ

‹‹መለመን›› የሚለው ቃል መልካም ነገር እንዲያደርግላቸው እግዚአብሔርን መጠየቅን የሚያመለክት ነው፡፡ ‹‹የቀናውን መንገድ›› የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሚጓዙበት ጊዜ ከክፉ እንዲጠበቁ ነው፡፡ በምንጓዝበት ጊዜ እኛ እና ልጆቻችን ንብረታችንም ሁሉ ከክፉ እንድንጠበቅ እግዚአብሔርን ጠይቀን ነበር››

የአምላካችን እጅ እርሱን በሚፈልጉ ሁሉ ላይ ነች

የእግዚአብሔር እጅ በሕዝቡ ላይ ናት የሚለው አባባል በሕዝቡ ላይ ያለውን የእግዚአብሔር እርዳታ ያመለክታል፣፣ እግዚአብሔርን መፈለግ እርሱን የማገልገል ምሳሌአዊ አነጋገር ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር እርሱን የሚያገለግሉትን ሁሉ ይረዳቸዋል››

ነገር ግን ኃይሉና ቁጣው እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው

የእግዚአብሔር ኃይልና ቁጣው በሕዝቡ ላይ ይሆናል የሚለው አባባል የሚያመለክተው እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚቀጣ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መርሳት እግዚአብሔርን ለማገልገል እምቢ ማለትን የሚያመለክት አባባል ነው፡፡

ስለዚህ ጾምን እግዚአብሔርንም ፈለግን

እዚህ ላይ እግዚአብሔርን ፈለግን ማለት አንድ ነገር እንዲያደርግልን እግዚአብሔርን ጠየቅን ማለት ነው፡፡ ‹‹ስለዚህ ጸምን እግዚአብሔር እንዲረዳንም ጠየቅነው››