am_tn/ezr/08/01.md

2.4 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ፡

ከዚህ ምዕራፍ ጀምሮ ግልጽ የሆነ የደረሲ ልዩነት እንመለከታለን፡፡ ከምዕራፍ 1-7 ጸሐፊው ስለ ዕዝራ የጻፈው ነው፡፡ ምዕራፍ 8 ግን ጸሐፊው ራሱ ዕዝራ እንደሆነ ያመለክታል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ከቁጥር 2-14 የመሪዎችና የአባቶቻቸው ስም ዝርዝር ነው፡፡ ሁሉም ወንዶች ናቸው፡፡

ከፊንሐስ ልጆች፣ ጌርሶን

በዝርዝሩ ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ ‹‹ነበር›› በሚለው ግስ መጻፍ ይቻላል፡፡ የፊንሐስ ዝርያ መሪ ጌርሶን ነበር›› ወይም ጌርሶን የፊንሐስ ዝርያ መሪ ነበር››

ከኢታምር ልጆች ዳንኤል

ይህ በስም ዝርዝር ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ የተጠቀሰ ነው፡፡ ይህም ‹‹ነበር›› በሚለው ግስ ሊጻፍ ይችላል፡፡ የኢታምር ዝርያዎች መሪ ዳንኤል ነበር›› ወይም ዳንኤል የኢታምር ዝርያዎች መሪነበር››

ፋሮስ

የዚህን ሰው ስም በዕዝራ 2፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡

ከዳዊት ልጆች ሐጡስ --- ፋሮስ እና ዘካርያስ

ይህ በዝርዝሩ ውስጥ ሦስተኛው ነው፡፡ ይህም ‹‹ነበሩ›› በሚለው ግስ ሊጻፍ ይችላል፡፡ ‹‹የዳዊት ልጆች መሪዎች ሐጡስ እርሱም --- ፋሮስ እና ዘካርያስ ነበሩ›› ወይም የዳዊት ልጆች መሪዎች ሐጡስ እና ዘካርያስ ነበሩ--- ሐጡስ ከፋሮስ --- ወገን ነበረ››

ሐጡስ፣ የሴኬንያ ዘር የነበረ፣ ከፋሮስ ነገድም የነበረ ነው፡፡

ይህ ‹‹ከዘካርያስ›› በኋላ ለብቻው ሊጻፍ የሚችል ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ ‹‹ሐጡስ የሴኬንያ ዝርያ ነበረ፡፡ እርሱም የፋሮስ ዝርያ ነው››

ከእርሱ ጋር በእርሱ የዘር ሐረግ የተመዘገቡ 150 ወንዶች ነበሩ፡፡

ከዘካርያስ ጋር በእርሱ የዘር ሐረግ የተመዘገቡ 150 ወንዶች ነበሩ››

150 ወንዶች

አንድ መቶ ሃምሳ ወንዶች››