am_tn/ezr/07/27.md

1.4 KiB
Raw Permalink Blame History

አገናኝ መግለጫ

ዕዝራ ንጉሥ አርጤክስስ በሰጠው ድንጋጌ ምክንያት እግዚአብሔርን ያመሰግናል᎓᎓

በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያሳምር ዘንድ ይህን ሁሉ በንጉሡ ልብ አስቀመጠ

በንጉሡ ልብ ነገሮችን ማስቀመጥ የሚለው አነጋገር የሚያመለክተው አንድን አሳብ ወይም ፍላጎት እንዲኖረው ማድረግን ነው ‹‹በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲያከብር አደረገው››

የእግዚአብሔር ቤት

ይህ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ነው

ለእኔ የቃል ኪዳኑን ታማኝነት አድርጎልኛል

‹‹ታማኝነት›› የሚለው ረቂቀ ስም ‹‹ታማኝ›› ወይም ‹‹የታመነ›› በሚል ሊገለጽ ይችላል፡፡ ‹‹ለእኔ ታማኝ የሆነው›› ወይም ‹‹ለእኔ የታመነው›› /ምሥጢራዊ ስሞችን ተመልከት/

እኔም በረታሁ

በረታሁ የሚለው ቃል የሚያመለክተው መበረታታትን ነው፡፡

በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ

እዚህ ላይ የእግዚአብሔር እጅ የሚያመለክተው ለዕዝራ ያደረገውን እርዳታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለረዳኝ››